Angebote für Frauen in Not

ወዲያውኑ እርዳታ እፈልጋለሁኝ !

በቀጥታ ከተደፈሩ ወይም ደግሞ የሕክምና እርዳታ ካስፈለግዎት፤ እባክዎን እነዚህን የአደጋ-ቁጥሮች ይደውሉ :
Polizei 110
Notruf 112

የሴቶች-መጠለያ፤በጉልበት ለተጠቁ ወይም ፍራቻ ለደረሰባቸው ሴቶች፤የአስቸኳይ-መጠለያ ነው። በአዲሱ የኑሮ ሁኔታዎ ውስጥ እስኪረጋጉ ድረስ፤በሴቶች-መጠለያ ውስጥ፤ጊዜያዊ ጥበቃ እና ድጋፍ ያገኛሉ።

በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች፤በቀን ለ24 ሰዓታት ያህል፤ሊያገኙን ይችላሉ:
069 / 43 05 47 66
069 / 63 12 61 4
069 / 41 26 79

የፍራንክፈርት-ማሕበሮች የሴቶች-መጠለያዎች (Frankfurter Verein) ከፍራንክፈርት እና ከሄሴን ክፍለሃገር ሴቶች ይቀበላሉ።

ነጻ ቦታ ካለን፤እርስዎን (እና ልጆችዎን) ወዲያውኑ መቀበል እንችላለን። ይህም በማንኛውም ጊዜ፤በምሽትም ሆነ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ነው።

ነጻ-ቦታ፤ሁልጊዜ አይገኝም። ሌላ የሴቶች-መጠለያ ወይም አስቸኳይ መጠለያ ማግኘት እንዲችሉ እንረዳዎታለን።

ተጨማሪ መረጃዎች፤በኛ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች FAQ (ጥያቄዎች እና መልሶች) ላይ ይገኛል።

ምክር ያስፈልገኛል፤


ስለ ችግርዎ ከሆነ ሰው ጋር መነጋገር ከፈለጉ፤እኛን በነፃ ሊያነጋግሩን ይችላሉ።

በነዚህ የስልክ ቁጥሮች በመደወል፤ የምክር ማዕከላችን ላይ መድረስ ይችላሉ :
069 / 43 05 47 66
0172 / 619 89 84

የስራ ሳዓታችን :
ከሰኞ እስከ ዓርብ፤ከ9.00 እስከ 17.00 ሳዓት፤

ምክር ከተፈለገ ነፃ ነው፤ከፈለጉም ማንነትዎ ሳይታወቅ ሊቀር ይችላል።

ለግል ምክክር፤እባክዎን ቀጠሮ ይያዙልን። ምክክሩ በእኛ አማካሪ ማዕከል ወይም በሌላ ቦታ ሊከናወን ይችላል። አስፈላጊ ሆኖ ካገኙትም፤አስተርጓሚ ልናዘጋጅላቸው አንችላለን።


የመስመር-ላይ ምክር

በአሁኑ ጊዜ ስልክ መደወል ካልቻሉ ወይም የመስመር-ላይ (ኦን-ላይን) ምክክር መምረጥ ይፈልጋሉ?
እባክዎ ኢሜል ይላኩልን፤E-Mail:

መልእክትዎ በቢሮ ሰዓት ውስጥ፤እና ከሚቀጥለው የስራ-ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይሰራል።

ከቢሮ ሰዓት ውጭ ማመከር

ምክር ለመስጠት፤ የፌደራል የእርዳታ መስመር፤Bundeshilfetelefon በየቀኑ ተዘጋጅልዎታል። በበርካታ ሌሎች ቋንቋዎችም ቢሆን፤በስልክ ምክር ለማግኘት በ’08000 116 016 ይደውሉ።

ከቢሮ ሳዓታችን ውጭ፤የመስመር-ላይ (ኦን-ላይን) ምክር እንዲሰጥዎት ይፈልጋሉ? የፌደራል ቴሌፎን Bundeshilfetelefon በተጨማሪም የኢ-ሜል እና የውይይት ምክር ይሰጣል።

Hilfetelefon Gewalt gegen Frauen

Diese Website verwendet keine Cookies.
Funktional
Marketing
Tracking
ImpressumDatenschutzerklärung